top of page

"ሳቋማ" የተሰኘው መድረክ

የ KG-12 STEM ትምህርቶችን እንዲሁም የቋንቋ ሥልጠናን የሚሰጥ ተማሪ-ተኮር መድረክ ነው። 

“ሳቋማ” በዩቲዩብ ቻናል ፣ በድረ-ገፅ እና በሞባይል አፕሊኬሽን አማካኝነት ተማሪዎችን የሚረዳ መድረካችን ነው። በይማሩ ላይ የ KG-12 STEM ትምህርትን እንዲሁም የቋንቋ ሥልጠናዎችን እየገነባን እንገኛለን ፡፡

 

እያደግን ስንሄድ የሙያ ትምህርት ፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የግል እድገትን የሚያግዙ ሌሎች መድረኮችን እንደምናካትት ተስፋ እናደርጋለን ፡፡

platform_twophones.png
platform_phone_with_player.png

​አጠቃቀሙ ቀላል 

የሳቋማ አፕሊኬሽን 

በስትሪሚንግ "streaming" ታዋቂ የሆኑት አፕሊኬሽኖች የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ጥቅም ላይ በማዋል አፕሊኬሽናችን ቀላል እና ብዙ ትምህርትዎችን የማስተላለፍ ብቃት ያለው ነው። ያለምንም ችግር ቪዲዮቻችንን ዳውንሎድ በማድረግ እንደፈለጉ መመልከት ይችላሉ።

 

አፕሊኬሽኑ ከጊዜ ጊዜ የሚሻሻል እና ከድርጅታችን ጋራ አብሮ የሚያድግ ነው። 

​ተደራሽነት ያለው

ሳቋማ በመረጃ መረብ 

በማንኛውም ስማርት የመገናኛ መስሪያዎች ሊጎበኝ የሚችል ሲሆን ትምህርትዎችን "ስትሪም" ማድረግ ይችላሉ።

2.png
platform_raspi.png

​ኢንተርኔት ባይኖርስ?

ኢንተርኔት አልባ የትምህርት ጣቢያ

የኢንተርኔት እና የዳታ ስርጭት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ተደራሽነት ይጎለዋል። ይሄንን ችግር ለመቋቋም እና የዲጂታል ትምህርትን ለሁሉም ለማድረስ በሌላ አይነት ቴክኖሎጂ እንጠቀማለን። 

​ትናንሽ ሰርቨርዎችን በተለያዩ ትምህርት ቤትዎች እና ተማሪዎች በሚገኙባቸው ቦታዎች በመግጠም ትምህርታችን ያለ ምንም ኢንተርኔት ዳውንሎድ እንዲደረግ ያስችላል። እነዚህ ሰርቨርዎች አጠቃቀማቸው ቀላል እና በቀላሉ የማይበላሹ ናቸው። 

bottom of page